Blog
 እግዚአብሔር ውለታ ሊውልልህ ሲፈልግ ሰዎች በማያወቁት ሸለቆ ያሳልፍሃል። ወንድሞችህ በጭካኔ አንተን ገፍትረውህ የጣሉበትን ጉድጓድ ጥልቀቱን እንኳን አያውቁትም ። በማያውቁት ሸለቆ ውስጥ ያሳልፍሃል ፤ በማያውቁት በረሃ ይመግብሃል ፤ በማያውቁት ማዕበል ውስጥ ያሳልፍሃል ፤ በማያውቁት ገደል ላይ ድልድይ ሆኖ ያሻግርሃል ፤ ለማያውቁት ብቸኝነትህ የልብ ወዳጅ ያጎናፅፍሃል። እነሱ ገፍትረው መጣላቸውን እንጂ ጉድጓድህን ፤ ሸለቆህን ፤ በረሃህን፤ ማዕበልህን፤ ብቸኝነትህን አያውቁልህም እግዚአብሔር ግን ሁሉን ያውቅልሃል አሳልፎልሃል። ሌሎች የሠጠሙበትን ማዕበል አንተ የተሻገርከው አስተዋይ ስለሆንክ ሳይሆን ጌታ ስለ ራራልህ ነው። መልካም ስለሆንክ ሳይሆን እግዚአብሔር ስላዘነልህ ነው። ዛሬ ላይ ሰው ሆነህ መቆምህ ለእነርሱም ጥቅም ስለሆነ እግዚአብሔር ስለ አንተ ብቻ ሳይሆን ስለ እነርሱ አይጥልህም። እግዚአብሔር አይደለም ከሌላው ከራስህ እንኳን ያድንሃል። ከመጣል መሃል እጅግ ክፉው መጣል ባለቤት ለሌለው ክፋት ተላልፎ መጣል ነው ። ቢያንስ ለሚደርስብህ ጥፋት ተጠያቂ ይኖራል ። የራስ ሰው ሲጥልህ ግን የወደቅህበትን አታውቀውም ስለዚህ አንተም ራስህን ትጥለዋለህ ፤ አየህ እግዚአብሔር ከዚህ እንኳን ነው ያዳነህ። በአንዳንድ የሕይወት መስመሮች ወድቀን የተነሳን ይመስለናል ግን ዞር ብለን ስናስተውለው ገና ሳንወድቅ በመንገዳገድ ላይ እያለን ነው ውዳችን የደረሰልን እና ያነሳን ። የወደቅን የመሰለን አወዳደቃችን እጅግ ሃይለኛ በመሆኑ ፤ መንገዳገዳችን ራሱ አስፈሪ በመሆኑ ነው። እግዚአብሔር እስክትወድቅ አይጠብቅም ቀድሞ ያነሳሃል! እግዚአብሔር ደግ ነው ። አንድ ነገር እናስተውል በማንም ጉድለት ማንም ሞልቶለት አያውቅም በማንም ሙላት ማንም ጎድሎበት አያውቅም ። ማንሳት ባንችል እንኳን አንግፋ መደገፍ ባንችል እንኳን አናሳድድ ማፅናት ባይሆንልን እንኳን አንጣል ። ጥሎ ማለፍ ለአለም እንጂ ለክርስትያን አይሰራም አብሮ ማለፍ ውዴታችን ብቻ ሳይሆን ግዴታችን ነው። 
      ከሁላችሁ የማንስ ታናሽ ወንድማችሁ ዲያቆን ሐዋዝ ተገኝ። የቅርብ ቀን አስተያየቶች :

 • Edn

  136 days ago

  እግዚአብሔር ሰላተ የተመሰገነ ይሁን, ጌታ ካተ ጋር ይሁን ወጣትነት ዘመንክ ይባረክ የረለምልም. እየባረኩ እባርክሀለው እያበዛው አበዛሀለው እንደሚል ለብዙ የምተርፍ ብዙ ያድርግህ ተባርከህ ለበረከት ሁን, አሜን🙏🙏🙏Related Posts


Leave for a comment


 • Latest posts


 • ያለፍከው !


  post-img

  እግዚአብሔር ውለታ ሊውልልህ ሲፈልግ ሰዎች በማያወቁት ሸለቆ ያሳልፍሃል።

  311 days ago
 • ያለፍከው !


  post-img

  ሌሎች የሠጠሙበትን ማዕበል አንተ የተሻገርከው አስተዋይ ስለሆንክ ሳይሆን ጌታ ስለ ራራልህ ነው።

  1343 days ago
 • አዲሱን ኪዳን ከእርሱ ጋር አድርጉ።


  post-img

  አዲሱን ኪዳን ከእርሱ ጋር አድርጉ። ዓለም እረፍት አልሰጠችኝም ፣ ብዙ አይነት ሃሳቦችን እና እምነቶችን እከተላለሁ ከሞት በኋላ ግን የት እንደምሄድ አላውቅም እያላችሁ የሞታችሁን ቀን በፍርሃት እያሰባችሁ ምትኖሩ ፣ ከሞት በኋላ የእግዚአብሔር እቅፍ ሳይሆን ሲዖል የሚታያችሁ ፣ እያደረጋችሁ ባላችሁት ኃጢአት ሕሊናችሁ ሰላም አጥቶ ዘወትር ጠላት የሚከሳችሁ ፣መዳን እፈልጋለሁ ፣ መቅበዝበዝ ሰልችቶኛል የምትሉ ኑ የሚወዳችሁ ጌታ አለ ፤ ኑ ከዚህ ሁሉ የሚያስጥላችሁ አዳኝ ጌታ አለ ፣ በክንፎቹ ጥላ ስር ማደር ይሆንላችኋል ኢየሱስ ክርስቶስ ይወዳችኋል። ይህንን የቃል ኪዳን ፀሎት አምናችሁ አብረን እንፀልያለን ... በቅንጣት ሰከንድ ውስጥ የዘመናት ሸክማችሁን እግዚአብሔር ከላያችሁ ያንከባልላል።

  1671 days ago
 • የጫካ ዜጎች


  post-img

  በአንድ ጫካ ውስጥ አንድ ከሺ ዓመታት በላይ እድሜ የጠገበ ዋርካ ነበረ፡፡ ዋርካው እጅግ ሰፊ፣ ውስብስብና ታላቅ ነው፡፡ በላዩ ላይ አዕዋፍ፣ በሥሩም እንስሳት ይጠለሉ ነበር፡፡ ከፊሉ ፍሬውን ከፊሉም ቅጠሉን ይመገባሉ፡፡ ሌሎቹም ግንዱንና ሥሩን ፍቀው ይበላሉ፡፡ አንዳቸው ለሌላቸው እንስሳትና አዕዋፍ የጠቀሙበት፣ አንዳቸውም አንዳቸውን የበሉበት ዘመን ነበር፡፡ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር የሚጋቡበት፣ አንዳቸውም ከሌላቸው ጋር የሚዋጉበት ዘመን አለ፡፡ ፈረስና አሞራ ተጋብቶ ክንፍ ያለው ፈረስ ተወልዶ ነበር አሉ፡፡ ታላላቆቹ እንስሳት በልተዋቸው ዘራቸው የጠፉ እንስሳትም አሉ፡፡

  1683 days ago